ለምን በኢትዮጵያዊነታችን መኩራት እንደሚገባን

… የቀጠለ

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ

ኢትዮጵያውያን እና ትወውልደ ኢትዮጵያውያን በሞላ በሚከተሉት ምክንያቶች በኢትየጵያዊነታቸው ሊኮሩ ይገባል፡፡ የኩራቶቹ ኹሉ ምክንያቶች ለመዘርዘር ጊዜ ስለሚፈጅ ጥቂቶቹ ብቻ ይቀርባሉ፡፡

 1. ኢትዮጵያ በሳይንስም ኾነ በመጽሐፍ ቅዱስ የሰወ ዘር መገኛ በመኾኗ፣
 2. ከ4500 ዓመታት በፊት በንጉሥ ሰብታህ አማካኝነት የጋዜጣንና የፖሊስን ሥራ ከዓለም ቀድማ ኢትዮጵያ ቀድማ በማቋቋሟ፣
 3. በዓለም ላይ የሌለ ከኖህ ጀምሮ ስሞቻቸውና የነገሡበት አዝማናት የተመዘገበ ነገሥታት በመኖራቸው፣
 4. አባታችን ኢትዮጵና እናታችን ሲና እንቁዮጵያግዮን መሢሁ ኢየሱስ ሲወለድ ልጆቻቸው ወደ እሥራኤል ተጉዘው ገዳ እንዳበረክቱለት እና በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው እና ጣና ጎጃም ላይ በተልእኮ በመሥፈራው፣
 5. ኢትዮጵና የእንቁዮጳግዮን ልጆች ታላላቅ ነገሥታት ኾነው በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በእስያ በመንሰራፈታቸው፣ ሥልጣኔያቸውን በማሠራጨታው እና መላውን አፍሪካ ኢትዮጵያ በማሰኘታው፣
 6. አፄ እስያኤል እስያ በሠልጣኑ በስሙ አኅጉሩን እስያ በማሰኘቱ፣ እጽዋትንና እንስሳትን አዳቅሎ አዲስ ውጤት ያስገኘው በዓለም የመጀመሪየው ‹ጀነቲክ ኢንጂነር› በመኾኑ፣ ከ3000 ዐመታ በፊት ይኸው ትልቅ ሰው ምናልባት በዓለም የመጀመሪያ የኾነውን ሰንደቅ ዓላማችንን በመፈልሰፉ፣
 7. ንግሥት ሳባ ትልቀቅነት… ኢትያኤል የተባለችው የሳባ ንግሥት በመጽሐፍ ቅዱስ ውሰጥ የተጠቀሰች፣ የዓለሙ ፈጣሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ስሟን ጠርቶ፣ የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበበኝነት ለመፈተን ኢየሩሳሌምን መገብኝቷን የመሰከረላት ትልቅ ሰው (ሴት) በመኾኗ፣
 8. በአፋሮች ትልቅነት… አፍሪካ በአፋሮች አፍሪካ ስለተባለች፡፡ ከ3000 ዘመናት በፊት አፋሮች ታላቅ መርከብ ገንቢዎችና መርከበኞች፣ እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅና በእሥራኤል ስመ ጥር የኦፊር ወርቅ ነጋደዎች ከመኾናቸውም በላይ ተጽእኖ አሳዳሪዎች በመኾናቸው፣ 
 9. የኢትዮጵያ ዝርያዎች 12 ጠበብት ነገሥታት ኾነው እሥራኤሎች የሚጠብቁት መሢህ መወለዱን ሳያዉቁ የእኛዎቹ ከሩቅ ኾነው የመሢሁን መወለድ ተረድተው ከኢትዮጵያ ተነሥተው በኮከብ እየተመሩ፣ ቤተልሔም ደርሰው ለመሲሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ገዳ በማቅረባቸው፣
 10. በዓለም ላይ ካሉት ነገሮች ኹሉ በጣም ውድና ብርቅ የኾነው የታቦቱ ማረፊያ እና መኖሪያ አድርጎ እግዚአብሔር ከእሥራኤል ይልቅ ኢትዮጵያን በመምረጡ፣
 11. ኢትዮጵያ በዳዊት መዝሙርና በሌሎችም የመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ውስጥ በእግዚአብሔር በመጠራትዋ፣
 12. እግዚአብሔር በታችን ኢትዮጵያውያን አይሁዳዊያንን በእግራቸው ስለማቆማቸው፣ ከነብዩ ከሙሴ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ አይሁዳውያንን ወደ ግዛትዋ እያስገባች ጥገኝነት፣ መሬትና ንግሥና ሳይቀር እየሠጠች አስተናግዳለች፡፡ በሌላ አገር ግን እሥራኤላውያንን ያሳድዷቸዋል፤ እንዲሁም ይገድሏቸው ነበር፡፡ በእኛ በጎ አድራጊነት እንኮራለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እሥራኤላውያን በባርነት በባቢሎን 70 ዓመት ሲሰቃዩ ቆይተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ቤተመቅደሳቸውን ካደሱ በኋላ መጻሕፍት አጡ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስንና ሌሎች ብርቅዬ መጻሕፍትን ኢትዮጵያ ስለላከችላቸው እንታበያለን፡፡
 13. ትልቅ ለሚባለው ለሙሴ ጥገኝነትና ሚስት ኢትዮጵያ ሰጥታ የፍትሕንና የሕግ አስተዳደርን፣ እንዲሁም ነገረ መለኮትን ስላስተማረችው፣
 14. ኢትዮጵያ በርካታ የሴት ነገሥታትን በኢትዮጵያና በግዛቶቿ ላይ ሾማ የሴቶችን መብት በማሰከበር በዓለም ግንባር ቀደም በመኾኗ፣
 15. ኢትዮጵያ ከጣና ሐይቅ ተነሥታ ወደ ኑቢያግብፅ ወርዳ፣ የግብፅንና የኑቢያ ሥልጣኔ በመፍጠሯ፣ ሕልቆ መሣፍት ወንዶች ፈርኦኖችን እና ህንድኬ በሚል ማረዕግ 17 የሴት ንግሥታትን በግብፅ፣ በሊብያ እና በኑቢያ ላይ በመሾሟ፣
 16. አፄ አክሱማይ የዓለም አባት፣ የነገሥታት ራስ ተብሎ ከባቢሎን ሳይቀር በንጉሦች ሳይቀር በንጉሦች የተበደሉ ዜጎች ለአቤቱታ ወደ እሱ ሲመጡ እንባቸውን ስላበሰላቸው፣
 17. ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ዮሴፍ በኢትዮጵያ ግዛት፣ በግብፅና በኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት አግኝተው በመኖራቸው፣
 18. ኢየሱስ ራሱን ለአይሁዳውያን ሳይገልጽ በ22 (ዓመት) ዕድሜው ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ለኛ ቅድሚያ ሰጥቶ ራሱን ለኛ ገልጾ እስከ 25 ዓመት ዕድሜው ድረስ ሲያስተ
 19. ምርና ሲፈውስ ሃገራችን ውስጥ በመኖሩ፣
 20. ኢየሱስ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ሲል ግብፅ ሳለ ጥገኝነት የሰጠውን ንጉሥ ኣማናቱ ተትናይን እግረ መንገዱን ጎብኝቶ ለአንድ ሣምንት እሱ እልፍኝ ውስጥ ሰንብቶ ነበር፡፡ ኢየሱስ ወደ ኢትዮያ ምድር እንደተሻገረ እልፍኙን ንጉሥ አማንቱ ተትናይ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወቱ እያለ እኛ በዓለም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያ በመመሥረታችን፣
 21. ንግሥት ህንደኬ ዣን በጅሮንድ በቅዱስ ፊሊጶስ መጠመቁና እሱ ከአውረፓውያን ቀድሞ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ በማስገባቱ
 22. አውሮፓውያን ወደ ክርስትና የተሸጋገሩት ከአረማዊነት ሲኾን ኢትዮጵያውያን ግን ከኦሪት ሃይማኖት ነው፡፡ ይህ በመኾኑም የክርስትና ዕውቀታችን ከአውሮፓውያ ለማጥለቅና ለማበልጸግ አስችሎናል፡፡ በዚህም እንኮራለን፡፡
 23. ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያውያን ውስጣቸው የኖርኩ ዘመዶቼ ናቸው፤ በእኔ ያምናሉ፤ እናንተ እነሱን ለማሳመን ሳትደክሙ አጥምቃችሁ አቁርቧቸው ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በርጠሎሚዎስን፣ ማቴዎስን፣ ቶማስን፣ ናትናኤልን፣ እንድርያስን እና ማርቆስን ወደ ኢትዮጵያ ልኳቸዋል፤ ከሃዋርያ ግምሾቹ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ስለአስተማሩ በእግዚአብሔር እንደተከበርን ስለሚሰማን፣
 24. ኢትዮጵያውያን ክርስትያናት እና አይሁዳውያን ያለደም መፋሰስ ተስማምተው የኦሪትን እና የክርስትናን አምልኮ የሚተውትን ትተው የተረፉትን ወደ ክርስትና በማስተላለፋቸው
 25. ከኢትኦጵ እስከ አፄ እስያኤል ድረስ የኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ የሚነጋገሩ ሊቀካህናት መኾናቸውና ፈሪሃ እግዚአብሔር ሕዝባቸውን በፍትሕ እና ርትህ በማስተዳደራቸው እና ይህ ክስተት በዓለም ላይ የሌለ በመኾኑ፣
 26. ነብዩ ሙሃመድ በችግር ላይ ሳለ ዘመዶቹን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ ኢትዮጵያ ጥገኝነት ስለሰጠቻቸው፣ መሃመድ ራሱ ሙስሊም ከመኾኑ በፊት፣ ኢትዮጵያ በመካና በመዲና ውስጥ የራሷ ቤተክርስቲያ ስለነበራት እና እሱ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተጠቃሚና የሊቀ ካህናቱ ወዳጅ በመኾኑ፣ እንዲሁም በመጀመሪያ አላህ አክበር ብሎ አዛን ያለው ድምፀ መረዋው ኢትዮጵያዊ ቢላል ሀበሽ በመኾኑ፣ ነብዩም ካልነኳችሁ ኢትዮጵያውያን ላይ ጀሃድ አታካሂድ፣
 27. ኢትዮጵያ መስሊሞችና ክርስቲያኖች በሃይማኖት ልዩነቶች ካለመጋጨታቸውም በላይ ተፋቅረውና ተባብረው ቤተክርስቲያኖች እና መስጊዶች አንዱ ለሌላው በመገንባታቸው፣ አብረው በመጸለያቸው እና ከተዋደዱ ያለብዙ ችግር መጋባት በመቻላቸው፣
 28. ኢትዮጵያውያ በዓለም ላይ የሌሉ ብርቅዬ የሱባ እና የሳባ ፊደላትን ፈጥረዋል፣
 29. እንደ አክሱም እና ላሊበላ ዓይነት ያልተለመዱ የሥነ ሕንፃ ውጤቶች መኖራቸው፣ ከኢትዮጵያ የተገኘው ቅዱስ ያሬድ ልዩ ማሕሌትን በመድረሱ እና ከአውሮፓውያን 700 ዓመታት አስቀድሞ የዜማ ምልክቶችን በመፈልሰፉ፣ እንዲሁም የማንንም የማይመስል ቅዳሴ እና ሥርዓተ አምልኮ ስለአለን፣
 30. በቀለማችን እና በተክለሰውነታችን የተቅለመለምን አበቦች ከመኾናችንም በላይ የተለያዩ አልባሳት፣ ዳንኪራዎች እና ባህላዊ ዕሴቶች ሰለአሉን፣
 31. ከተለያዩ የምግብ አሠራር ሙያዎች በተጨማሪ ለዓለም ያበረከትናቸው እንደ ቡና እና ጤፍ አዝርእት ስለአሉን፣
 32. ኢትዮጵያ፣ ባለፉት 4000 ዓመታት ሮማውያንን፣ ግብፆችን፣ ዐረቦችን እና ሌሎችንም በጦርነቶች ድባቅ እየመታች ነጻነታችንን እና ክብራችንን በማስጠበቋ እና ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች ኹሉ የነጻነት እና የድል አድራጊነት ዐርማ በመኾናቸውም በላይ አንዳቸውም ባለመማረካቸውና ጠላት እራሳቸውን እንኳን ለመያዝ ባለመቻሉ ደጋግመን እንኮራለን፣
 33. ቀጥሎም፣ እጅግ የሚያኮራን በኢየሱስ ክርስቶስ የደም ሥር ውስጥ የእኛ የኢትዮጵያውያን ደም መፍሰሱ ነው፡፡ እንዴት ቢሉ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱስ ዳዊት ዘር በመኾኑ እና የእሱም እናት አይሁዳውያን አዶልያ ወይም አዴል የሚሏት፣ እኛ ደግሞ ሀብሌ የምንላት ኢትዮጵያዊት በመኾኗ፣
 34. በመጨረሻም በቅድመ ወላጆቻችን ክህነታዊ ማዕረግና ክብር እንኮራለን፡፡ እግዚአብሔር ኹለት ዓይነት የክህነት ማዕረግ ሰጥቶአል፡፡ አንደኛው ዝቅተኛው እና ለዐይሁዳውያን ብቻ የሰጠው የአሮን ክህነት ሲኾን ኹለተኛው እጅግ ከፍተኛው ለኢትዮጵ አባት ለሳሌሙ ንጉሥ ለመልከጸዴቅ ያቀደው ነው፡፡ የአሮን ሹመት ካህነት ብቻ ሲኾን የመልከጸዴቅ ግን የንጉሠ ነገሥትነት እና የካህንነት ነው፡፡ መለኮታዊና ዓለማዊ ማዕረግ ነው፡፡ ራዕየ ዮሐንስ እንደሚተነብይልን የዓለሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደፊት በመልከጸዴቅ ሥርዓት የካህን ካህን (ሊቀ ካህናት)፣ የንጉሥ ንጉሥ (ንጉሠ ነገሥት) ኾኖ በኢየሩሳሌም ላይ የራሱን ምድራዊ መንግሥት መሥርቶ ይነግሣል፡፡ በዛም ጊዜ አባታችን ሆይ መንግሥትህ ይምጣ፣ ብለን የየጸለይነው ይፈጸማል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ክህነትና ንግሥና በአባቶቻችን በመልከጸዴቅ፣ በኢትዮጵያ እና በልጆ ሥርዓት ስለኾነ እጅግ እንኮራለን፡፡

የሚያኮሩንን ኹሉ ነገሮችን በእርግጥ ዘርዝረን አንጨርሰውም፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ከላይ የሠፈሩት ናቸው፡፡ እነሱን መስፈንጠሪያ አድርገን፣ ደረታችንን ነፍተን፣ በኢትዮጵያዊነታችን ታብየን፣ እርስ በርሳችን ተከባብረን፣ ተፋቅረን እና ተቃቅፈን በእኩልነት ወደፊት እመር እንላለን፡፡ እንግዲህ ጥንታዊ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ትልቅ ከነበሩ፣ እኛም የእነሱን አርአያ እና ፈለግ ተከትለን  በመነሳሳት ወደፊት ትልቅ የማንኾንበት ምክንያት የለም፡፡

(ስውሩና ያልተነገረው የአይሁዳውያን እና የኢትዮጵያውያ ታሪክ፤ ገጽ 222-233)

Please follow and like us:
error

Leave a Reply