መኪናው ሥልጣን

(በካሣሁን ዓለሙ)
ሥልጣን መኪና ነው- የሕዝብ መገልገያ፣
አንዱ ትቶ ሲወርድ- ለአንዱ መሣፈሪያ፤
መሪውም ሹፌር ነው- መኪና እሚነዳ፣
መጠንቀቅ ያለበት- ሕዝብ እንዳይጎዳ፡፡
ተሣፋሪዎቹም- የመኪና ወንበር፣
በሥልጣን ማገልገል በሌላ እስኪቀየር፤
በመጠንከር ይሥሩ- ትተው መሰባበር፡፡
የመኪናው በርም- በያለበት ሥፍራ፣
የሥልጣን ክፍፍል፣
በግልፅ እየታየ- በተጠይቆ ይሥራ፡፡
መብቶችም ያክብር- ይህ ሥልጣን መኪና፣
መንገዱ በሙሉ ሥርዓት አስከባሪ- ትራፊክ ነውና፤
ሥርዓት ጠባቂም- ከመኪና ውጭ፣
መኪናው ሰዎችን- ውል ስቶ እንዳይገጭ፣
የመንገድ ትራፊክ- ሲቪል ማኅበራት፣
ትራፊክ መብራትም- ፍተሐ- ፍርድ ቤት፣
ገለልተኛ ኾነው- በሥርዓት ይምሩት፡፡
ማቆሚያም ይኑረው- ማረገፊያ ሥፍራ፣
የመውጫ መዉረጃ- የጊዜ ፌርማታ፤
ሕዝብም ይስማማበት- በመኪናው ሥራ፣
ሳሳፍር/ሳይሳፈር ቀርቶ- ሌላ እንዳያወራ፡፡
እንግዲህ በሥልጣን- ወጥታችሁ ስትሄዱ፣
ሥርዓቱን ኹሉ- አክብሩ ተረዱ፤
በተለይ በተለይ ሥልጣን መኪነውን-
ይዛችሁ ስትነዱ፡፡
(19/09/93 ድባብ መናፈሻ)

Please follow and like us:
error

Leave a Reply