ቀላይን በማንኪያ- ሊቃውንት በስቅለት ዙሪያ ከተቀኟቸው ቅኔዎች

 

በካሣሁን ዓለሙ

 

1. ግእዝ ክብር ይእቲ

 

ተመነየ ሞተ አምላክ ኖላዊሆሙ፣

ለአዳም ወሔዋን አባግዒሁ ኩሎሙ፣

አርዌ እኩይ እስመ በልዖሙ ቀዲሙ፣

ቄጽለ ቄጽለ እንዘ ይሬእዩ በዐይኖሙ፡፡

ትርጉም፡-

እርኛቸው አምላክ ሞትን ተመኘ፣

ሁሎቹን በጎች አዳምና ሄዋንን በአይናቸው ቅጠል ቅጠልን ሲያዩ

ክፉ አውሬ ቀድሞ በልቷቸዋልና፡፡[1]

 

2. ሕንጽሃ (ቅኔ)

እንከ ቀራንዮ ኢይበጽሕ እግእነ

እስመ ቀራኒዮ ምድረ ደም ኮነ፡፡

ትርጉም፡-

እንግዲህ ጌታችን ቀራኒዮ አይደርስም

ቀራኒዮ የደም መሬት ሆኗልና፡፡[2]

 

3. ዕዝል ጉባኤ ቃና

 ለበሊዕ ኅብስተ ሮምያ መስቀለ

ቦአ ቃል እንግዳ ዐውደ ቀራኒዮ መርጡለ፡፡

ትርጉም፡-

የሮሚያን እንጀራ መስቀልን ለመብላት

ቃል እንግዳ ወደ ቀራኒዮ አደባባይ ቤት ገባ፡፡[3]

 

4. ግእዝ ክብር ይእቲ

(መምህር አባ ገሪማ ዘገብረ ማሪያም፣)

 

ዘመደ ሥቃይ አኀዘ እደዊሁ

ዘሐመ ወልድ ሕማመ አዳም አቡሁ፤

ወገሠሠት እም ኩናተ ሐፂን ገባሁ፤

ሕማመ ሥቃይ ግሩም እስመ ጸንዐ ላዕሊሁ፡፡

ትርጉም፡-

የሥቃይ ዘመድ ችንካር የአባቱ አዳም ሕማምን፣

የታመመ የወልድ እጆቹን ያዘ፤

እናት የብረት ጦርም ጎኑን ዳሰሰች፤

አስፈሪ የሥቃይ ሕመም በእሱ ላይ ፀንቷልና፡፡[4]

 

5. አጭር ኩልክሙ

አስቄቀየ ወልድ ዕፄ መቃብር በቃሉ፣

እስመ ይመስሎ ዘይትበላዕ ኩሉ፡፡

ትርጉም፡-        

የመቃብር ትል ልጅ በቃሉ አለቀሰ፣

ኹሉ የሚበላ ይመስለዋልና፡፡[5]

 

6. ዘአምላኪየ

በቀራኒዮ ተገብረ ዘያስተዓጽብ ልሂቀ፣

እንዘ ደም አልቦ በኮኮብ ዘወድቀ

ዘኢይወድቀ ወርኅ አምጣነ በደም ተጠምቀ፡፡

ትርጉም፡-

ሽማግሌን የሚያስደንቅ በቀራኒዮ ተደረገ፤

በወደቀ ኮኮብ ደም ሳይኖር

ያልወደቀ ጨረቃ በደም ተጥለቅልቋና፡፡[6]

 

7. ዘአምላኪየ

አናኒ አምላክ ዘኢይትዐወቅ ሀገሩ

አነመ ልብሰ ተቀንዎ በእዱ ወእግሩ፤

አዳም ወሔዋን ደቂቁ እስመ በተዐርቆ ነበሩ፡፡

ትርጉም፡-

ሀገሩ የማይታወቅ ሸማኔ አምላክ

በእጅና በእግሩ ልብስ መቸንከርን ሠራ፤

ልጆቹ አዳምና ሔዋን ተራቁተው ነበርና፡፡[7]

 

8. ግእዝ ጉባኤ ቃና

(ዘእሜቴ ገላነሽ)

 

መርገመ ጾመ መድኃኔዓለም ሠዐርከ፣

አኮኑ ሐሞተ ዘምስለ ሥጋ በላዕከ፡፡

ትርጉም፡-

መድኃኔዓለም ጾም/መርገምን ሻርህ፣

ሃሞትን ከሥጋ ጋር በልተሃልና፡፡[8]

 

9. እዝል ጉባኤ ቃና

ሕፁረ ቅንዋት አሥዋክ ጽጌ ማርያም ረዳ፣

በማህዋወ መስቀል ተሠይመ ለኢየሩሳሌም በዐውዳ፡፡

ትርጉም፡-

በእሾሆች ችንካሮች የታጠረ የረዳ ማርያም አበባ

በኢየሩሳሌም አደባባይ በመስቀል ብርጭቆ ተዘጋጀ፡፡[9]

 

10. ዋዜማ

ዘምሥራቅ (አለቃ ዘኤልሻማ)

 

ይቤሎሙ ለአኃዊሁ፣

በግዕ ወላህም እለ ወፈሩ ቀላየ፣

ኀያል ጾመ ኢየሱስ ዘኩሎ ቀነየ፣

ዘይፈለክፈክሙ መኑ እንዘ ሀሎኩ ለልየ፣

ባሕቱ እንዳኢ ለክሙ እምድኅረ ሞትየ፣

እሰመ ሀሎ ፋሲካ ፀርየ፡፡

ትርጉም፡-

ሁሉን የገዛ ኃይለኛ ኢየሱስ ጾም፣

ወደ ወንዝ የተሠማሩ

ወንድሞቹን በግና ላምን

‹እኔ እያለሁ የሚነካችሁ ማነው?› አላቸው፤

ነገር ግን ከሞቴ በኋላ እንጃላችሁ!

ጠላቴ ፋሲካ አለና፡፡[10]

 

11. ሚበዝኁ

ዘገብረ ሥላሴ ክንፉ (ዘኤልያስ)

 

ማእዜ ረከበ፣

ወርኅ ሰማያት ትዝምደ ዘምስለ አይሁድ አይሁድ

እምድኅረ ይቤሉ ይኩን ላዕለ ውሉድነ ደመ ወልድ፤

አኮኑ ተግህደ ትእምርተ ቀይህ ደም በዘወርሀ ሰማይ ዐውድ፡፡

ትርጉም፡

የሰማያት ጨረቃ ከአይሁድ ጋር ዝምድናን መቼ አገኘ?

አይሁድ የወልድ ደም በልጆቻችን ላይ ይሁን ካሉ በኋላ

የቀደም ደም ምልክት በሰማይ ጨረቃ ዙሪያ ተከስቷልና፡፡[11]

 

12. ዘአምላኪየ

(ዘዋሸራ ተክሌ)

 

በቀራንዮ ተገብረ፣

ዘያስተአጽብ ልሒቀ፤

እንዘ ደም አልቦ በኮከብ ዘውድቀ፤

ዘኢወድቀ ወርኀ

አምጣነ በደም ተጠምቀ፡፡

ትርጉም፡-

በቀራንዮ ሸማግሌን የሚያስደንቅ ታምራት ተደረገ፤

 በወደቀው ኮከብ (ሰው) ደም ሳይኖር

 ያልወደቀው ጨረቃ (ሰው) በደም ተጠምቋልና፡፡[12] 

 

13. ሚበዝኁ

(ዘዋሸራ ተክሌ)

 

ሐሜተ ክልኤቱ አኀው

ዘኢፈርሀ ወልድ፣

በልዐ በተክብቶ፤

ሥጋ ንጹሐ እንዘ የአጹ ኆኅቶ፤

ወፍሉጠ ሞት ኮነ፣

ባህቲቶ ዘበልዐ፣

እስመ ይመውት ባሕቲቶ፡፡

ትርጉም፡-

የሁለት ወንድሞቹን ሐሜት ያልፈራ ወልድ

 ደጃፉን ዘግቶ ተሸሽጎ ንጽሕ (የሚጣፍ) ሥጋን በላ፤

 በሞትም የተለየ ሆነ ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታልና ፡፡[13]

 

14. ዋዜማ

በከየ ያዕቆብ

ጊዜ ሞተ ዮሴፍ ወልድ፣

በልብሰ ዮሴፍ ዋሕድ፤

ለሰብእ አኮኑ ከመዝ ልማድ፣

ባሕቱ ድንግል

ርኅቅተ ቅሩብ ዘመድ፤

በምንት ትበኪ

ጊዜ ሞተ ወልድ፤

እስመ ልብሶ ወሰዱ አይሁድ፡፡

ትርጉም፡-

ያዕቆብ ዮሴፍ ልጁ በሞተ ጊዜ በአንድ ልጅ ዮሴፍ ልብስ አለቀሰ፤

 የሰው ልማድ እንደዚህ ነውና፤

ነገር ግን የቅርብ ዘመድ ሩቅ የሆነች ድንግል ወልድ በሞተ ጊዜ በምን ታለቅሳለች?

ልብሱን አይሁድ ወስደውታልና፡፡[14]

 

15. ሥላሴ ቅኔ

ሕዝበከ ለተራድኦ፣

እፎ አርመምከ ዕፀ መስቀል፣

ዘኢለቅሁኑ እክለ፤

ወእፎ መሐሪ ልቦናከ ክህለ፤

ዕፀ ምድር ዐረብ ጥቀ ታሕቴሃ፣

እመ ሕዙነ ልበ አጽለለ፤

ትበኪ ቄጽለ ወሐመልማለ፤

ወኀዘን ላዕሌሃ፣

ለእመ ኀየለ፤

አዕጹቂሃ ይትላፀዩ ቄጽለ፡፡

ትርጉም፡-

ዕፀ መስቀል ሆይ ወገኖች ያላበደሩን እህልን ሲካፈሉን እንዴት ዝም አልህ?

 መሐሪ ጌታስ እንዴት ልቦናህ ቻለ?

የዓረብ እንጨት ስንኳን የልብ አዘነተኛ ከበታችዋ በተጠጋ ጊዜ ቅጠልን ታለቅሳለች (ታረግፋለች)፤

 ኀዘን በላይዋቢጸናባትም ጫፎቿ ቅጠልን ይላጫሉ (ያረግፋሉ)፡፡ [15]

 

17. ክብር ይእቲ ቅኔ ዕዝል

(ዘመምህር ይኄይስ ወርቁ)

 

ፍኖተ መስቀል ጌሠ እግዚእነ

መስተፅእነ ፈረስ ተሰብኦ፤

እንዘ ስንቀ ዕለት ይነሥእ

ተረፈ ኦርዮ ተገፍዖ፡፡

ትርጉም፡-

ፈረስ ሰው መሆንን የጫነ (በፈረስ ሰው መሆን የተቀመጠ) ጌታችን ኢየሱስ

ከኦርዮ የተረፈ ምግብ ተገፍዖን የዕለት ስንቅ ይዞ

የመስቀል መንገድን (መስቀል መንገድን) ገሠገሠ፡፡[16]

 

18. ሚበዝሁ

(መምህርአክሊሉ ወርቅነህ፣ ዘደበጋ ሚካኤል ደንበያ)

 

በይነ ጣዕዋሃ ሐንካስ፣

ትትበላዕ ላሕም አአምሥጦ ዘይትከሃል

ወለዘተበልዐት ላሕም መድኃኔ ዓለም ተመሰላ፣

አኮኑ ተቀትለ በዘበልዐት ሔዋን ፍሬ ዕፀ በለስ ሰግላ፡፡

ትርጉም፡-

ማምለጥ የሚቻላት ላም፣

ስለ አንካሣ ጥጃዋ ተበላች፤

የተበላችውንም ላም መድኃኒያዓለም ተመሰላት፣

ሔዋን የሾላ ፍሬ ዕንጨትን በበላች ተገድሏልና፡፡[17]

 

  18. ዕዝል ጉባኤ ቃና

አይሁድ እግዚአ ኢረሰይዎ ለወልደ አምላክ ልዑል፣

እስመ ምስለ ኖሎት ይመውዕል እንዘ ይሰክብ በጎል፡፡

ትርጉም፡-

አይሁድ የልዑል አምላክ ልጅን ጌታ አላደረጉትም፣

በበረት እየተኛ ከእረኞች ጋር ይውላልና፡፡[18]

 

19. ዕዝል  ጉባኤ ቃና

(ዘመምህር ይኄይስ ወርቄ)

 

ከዋክብት ሕዝብ ይሰግዱ፣

ለሥዕለ አድኅኖ ስቅለት፤

እስመ ሠዐላ ጠቢብ ፈጣሪ

በልብሰ ማርያም ትስብእት፡፡

ትርጉም፡-

ከዋክብት ወገኖች ለማዳን ሥዕል ስቅለት ይሰግዳሉ፤

ጥበበኛ ፈጣሪ ልብሰ ማሪያም በተባለ ቀለም ሰውነት (ሥጋ) ሥሏታልና፡፡[19]

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


[1] የግእዝ ቅኔያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 1፣ ገፅ-147

[2] የግእዝ ቅኔያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 1፣ ገፅ- 352  

[3] የግእዝ ቅኔያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 2 ገፅ 26

[4]የግእዝ ቅኒያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 3፤ ገፅ 3

 

[5] የግእዝ ቅኔያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 2 ገፅ 33

[6] የግእዝ ቅኔያት የሥነ ጥበብ 1 ቅርስ ገፅ 277

[7] የግእዝ ቅኔያት የሥነ ጥበብ ቅርስ ገፅ 260

[8] የግእዝ ቅኒያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 3፤ ገፅ 187

[9] የግእዝ ቅኒያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 3፤ ገፅ 281

[10] የግእዝ ቅኒያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 3፤ ገፅ 228

[11] የግእዝ ቅኒያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 3፤ ገፅ 287-8

[12] መምህር ይኄይስ ወርቄ፣ ንባብ ወትርጓሜ ዘቅኔያት አዕማደ ምሥጢራት ገጽ 32

[13] ዝኒ ከማሁ፣ ገጽ 35

[14] ዝኒ ከማሁ፣ ገጽ 40

[15] ዝኒ ከማሁ፣ ገጽ 49

[16] ዝኒ ከማሁ፣ ገጽ 79

[17] የግእዝ ቅኒያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 3፤ ገፅ 7

[18] የግእዝ ቅኔያት የሥነ ጥበብ ቅርስ 2፣ ገፅ 37

[19] መምህር ይኄይስ ወርቄ፣ ንባብ ወትርጓሜ ዘቅኔያት አዕማደ ምሥጢራት ገጽ 27

Please follow and like us:
error

Leave a Reply