ተሐድሶ እንዴት ይታያል?

አያቶች፡-…

አባቶች… ጥበብ ዕድሜያቸውን ገብረው፣

የጎጆ ንድፍ ሲያበጁ፣

አረጁ… ዘመናቸውን ፈጁ…

ልጆች!

ጎጆውን ለመውረስ ሳይከጅሉ፣

እንዲህ አሉ….

‹ያባቶቻችን ጎጆ

ይሁን ባዶ ይሁን ኦና

በኛ መጠን አልተቀለሰምና፡፡..›

(በዕውቀቱ ሥዩም)

ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ የተሐድሶ ጉዳይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አነታራኪ ሆኗል፡፡ ንትርኩም ባፍ በመጣፍ እንደሚባለው ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡ ይህም በተለለያዩ ድራተ ገጽ፣ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ መጽሐፎችና ቴሌቪዥን ጣቢያዎችም እየተገለጸ ቆይቷል፡፡ ጭቅጭቁ ደግሞ ተሐድሶ የሚባለው እንቅስቃሴ አለ ወይስ የለም ከማለት ይጀምራል፡፡ እኔም ከዚህ  ‹እውን የተባለው የተሐድሶ እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ እየተካሔደ ነው? ወይም አለ?› ብዬ በመጠየቅ ልነሳ ፈለኩ፡፡

የዚህ ጥያቄ መልስ ‹የለም› የሚል ቢሆን ኖሮ የተባለው ሁሉ ስህተት ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ መነታረክ አያስፈልግም ነበር፡፡ በ‹ሌለ› ጉዳይ ላይ መነታረኩ ምን ጥቅም ይኖረዋል? በሌለ ነገር ያለው ‹የለም› የሚለው ስም ብቻ ነው፡፡ ባይሆን አንድ ነገር በአግባቡ መታየት ይኖርበታል ‹እና በእንቅስቃሴው ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፎች፣ መጽሔቶች፣… ከየት አምጥተውት ነው መነጋገሪያ ያደረጉት?›

እኔ በግሌ፡-

1)  ይህንን እንቅስቃሴ ከሚያካሒዱ ሰዎች ጋር በካል ተገናኝቻለሁ

2)  ቤተክርስቲያን ለማደስ በሚል የተዘጋጁ ከ10 ያላሰነሱ መጻሕፍትንና የተወሰኑ መጽሔቶችን አግኝቼ ተመልክቻቸለሁ፤ በግብረ መልስ የተጻፉ ጽሑፎችንም እንደዚሁ

3)  የተሐድሶን እንቅስቃሴ ለማጋለጥ በሚል ወይም እንቅስቃሴውን በመደገፍ የተለቀቁ ማስረጃዎችን በተለያዩ ድራተ ገጻትን አይቻለሁ

እነዚህን ማስረጃዎች ተመልክቼ መኖሩን ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ስለዚህ ተሐድሶ የሚባለው እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የለም ብሎ የሚከራከረኝን በጥርጣሬ ለማየት እገደዳለሁ፡፡ በዚህ የተነሣ የሚከራከረኝ ሰው ከሚከተሉት ሦስት ቡድኖች በአንደኛው ውስጥ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡

1)  ምናልባት በቤተ ክርስቲያኒቱ ያለውን ነበራዊ እንቅስቃሴ አያውቅም፤ የተሐድሶ እንቅስቃሴንም ባለማወቁ በድፍኑ ‹የለም› ሲባል ሰምቶ ያንን በመያዝ በጭፍን ያወራል፤

2)  እንቅስቃሴው መኖሩን ቢያውቅም የቤተ ክርስቲያኒቱ ስምና ክብር እንዳይጎድፍ እንቅስቃሴውን ሸፍኖ በመያዝ በምሥጢርነት ማቆየት ፈልጓል፤ ስለዚህ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ‹የለም› የሚለውን ሐሣብ ያራምዳል፤

3)  ‹የለም› በሚል ሽፋን እንቅስቃሴው ውስጥ ለውስጥ እንዲከናወን የሚያደርግ ሰው ነው፡፡

ከነዚህ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን ክፍሎች መካከልም የመጀመሪያዎቹ ችግራቸው የመረጃ እጥረት ነው ማለት ይቻላል፤ ስለዚህ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መኖሩን በትክክል የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካገኙ አቋማቸውን በመቀየር ‹የተሐድሶ እንቅስቃሴ መኖሩን› አምነው ለመቀበል አይቸገሩም፡፡ ችግራቸው ባለማወቅ ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በማወቅ መፍትሔ ያገኛል፡፡ ሁለተኛው ጎራ የሚገኙት አጉል ቀናነትና የዋህነት አለባቸው፡፡ እሳትንም በጭድ በመሸፈን ሊያጠፉ ይሞክራሉ፡፡ ስለዚህ የችግሩ ዕድሜ ማራዘሚያ ለመሆን ይገደዳሉ፡፡ የሐድሶ እንቅስቃሴ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር መሆኑን ካመኑ ችግሩን ሳያስወግዱ ማቆየት ውስብስብ ችግርን መጋበዝ እንጂ መፍትሔ አያስገኝም፡፡ ሦስተኛው የተሐድሶ አንቅስቃሴ አካል ነው፡፡ ስለዚህ የማታለል ሥራ ነው የሚያከናውነው፤ የተሐድሶ እንቅስቃሴም ስውር አካሔድ ማሳያ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በተለይም የቤተ ክርስቲያኒቱን መድረክ ለማስተማሪያነት የሚጠቀም ሰው የተሐሶ እንቅስቃሴ መኖሩን አያውቅም ለማለት ያስቸግራል፡፡

እሺ! ተሐድሶ የለም በማለት የሚከራከሩት በዚህ መልክ በሦስት ከፈልናቸው ታዲያ በምን እንለያቸው? ትልቁ ጥያቄ እዚህ ላይ ነው፡፡ ይህም ራሱን የቻለ የመፍትሔ አቅጣጫ መቀየስ እንዳለበት ይነግረናል፡፡ ይህ ከሆነም መፍትሔውን ለሌሎች አካላት (ለአባቶች) ወይም ለቤተ ክርስቲያን ልጆች ጥረትና መረጃን በአግባቡ የመያዝና የማሳወቅ ሥራ፤ እንዲሁም ትብብርና ቤተ ክርስቲያኒቱን የመጠበቅ  ኃላፊነት እንተወውና ወደ ሌላ ነጥብ እንሸጋገር፡፡

‹የተሐድሶ እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያኒቱ መኖሩ እርግጥ ከሆነ ምንጩ ከየት ነው? ከውስጥ ወይስ ከውጭ? ከውስጥ ነው የሚባል ከሆነ የትኛውን የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ መርህ ነው አድሳለሁ የሚለው? ለማደስ ያነሳሳው ምክንያትስ ምንድን ነው? ምክንያቱስ አግባብንት ያለውና በቂ ነው? እሺ ይሁን ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማደስም በቂና አግባባዊ ምክንያትም ይኑረው አካሔዱስ ትክክል ነው ወይ?…› እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች አጥጋቢና አዎንታዊ መልስ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ያለበለዚያ የተሐድሶው እንቅስቃሴ ችግር አለበት፡፡

በተቃራኒው ከውጭ ከሆነም ከየትኛው ቤተ እምነት እንደፈለቀና ይህንን ሊያደርግ የቻለበት ምክንያትና አካሔዱ ተለይቶ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ አይ! ሁለቱም (ከውስጥና ከውጭ) በመተባበር የሚያከናውኑት እንቅስቀሴ ነው ከተባለም እንዴት? የሃይማኖት ልዩነት የለም ማለት ነው? ይህ ከሆነስ በጥንት ጊዜ የተደረጉ ጉባኤያት ስህተት ናቸው ማለት ይሆን? ይህንንስ ለማድረግ የሚያስችል አሳማኝ ነገር ከምን ተገኘ? … › እነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ገባቸው ተመርምሮ መታየት አለበት፡፡
ወደ መጀመሪያው ተመልሰን ‹ይህ የተሐድሶ እንቅስቃሴ የተነሣው ከቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ከውስጥ ሊሆን ይችላል› በሚል ግምት ላይ እንነሣ፡፡ እሺ ከሆነ እንቅስቃሴ የሚያደርገው ምኑን ለማደስ ነው? ዶግማዎቿን? የቀኖና ሥርዓታቷን? ወይስ በታሪክ አመጣጧ ችግር ተፈጥሮ? ነው ከዚህ ከተባሉት አማራጮች ሌላ ምክንያት ይኖራል?› የሚሉ ጥያቄዎችን ለማንስት እንገደዳለን፡፡

ምክንያቱም እንቅስቃሴ የሚደረገው የሃይማኖት ዶግማዎቿን ለመቀር ከሆነ ግቡ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን በሌላ ለመቀየር ነው ማለት ነው፡፡ የአንድ የሃይማኖት ዶግማ ለዘላለም አይቀየርም፤ ዶግማው ከተቀየረ ሃይማኖትነቱ ተለወጠ ማለት ነው፡፡ የኢ/ኦ/ተ/ቤ የምትመራባቸው አምስት አዕማደ ምሥጢራት (ምሥጢረ-ሥላሴ፣ ምሥጢረ-ሥጋዌ፣ ምሥጢረ-ጥምቀት፣ ምሥጢረ-ቁርባን እና ምሥጢረ-ትንሣኤ ሙታን) አሏት፡፡ ከእነዚህ አንዱ ከተቀየረ እሷነቷን ታጣለች፡፡ ስለዚህ የሚካሔደው የተሐድሶ እንቅስቃሴ የቤተ ክርስቱን ዶግማዎች ለመቀየር ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት ያለመ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ደግሞስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማ ለማስቀየር የሚያስችል ሌላ ዶግማ ከየት ተገኘ? ለምንስ መቀየር አስፈለገ? እንቅስቃሴው የቤተ ክርስቲያንቱን ዶግማዎች ለመቀየር ከሆነስ ለምን ተሐድሶ ይባላል?…. በዚህ ዙሪያ ብዙ ጥያቄዎችን በማንሳት መተንተንና አንድምታቸውንም ማሳየት ይቻላል፡፡ ይሁንና በጥቅሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማዎች (አዕማደ ምሥጢራት፣ መሠረታዊ እምነቶች) መቀየር ቤተ ክርስቲያኒቱን ማጥፋት ነው፡፡ የተሐድሶ እንቅስቃሴም ‹ዶግማ ተኮር› ከሆነ ለማደስ ሳይሆን ለመቀየር ያለመ ነው ለማለት እንገደዳለን፡፡ ሥርዓትዎቿን ለማሻሻል ያለመ ከሆነስ?

የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓታት የዶግማ ማስፈጸሚያ ሥልቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ መጠመቅ የግድ ነው፡- ዶግማ ነው፤ የአጠማመቅ ሁኔታ ግን ሥርዓት ነው፡፡ ቁርባን ዶግማ ነው፤ ‹እንዴት መቁረብ ይኖርብናል?› በሥርዓት መልስ ያገኛል፡፡ በዚህ ዓይነት ከሐዋሪያት ጀምሮ ያሉ አባቶች ከኅብረተሰቡ የአኗኗር ሁኔታ ጋር የሚስማሙና ለጽድቅ ሥራ የሚያበቁ የእምነት መተግበሪያ ስለቶችን ነድፈዋል፤ እንደሁኔታውና እንደኅብረተሰቡ እያዩም ሊያስተካክሉት ይችላሉ፡፡ ለዚህም ልክ እንደ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ቤተ ክርስቲያኒቱ የምታሻሻልበት የራሷ ሥርዓት አላት፡፡ የተሐድሶም እንቅስቃሴ በዚህ ዙሪያ ከሆነ በሥርዓቱ መሠረት ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ባይሆን ‹የትኛውን ሥርዓት ነው እንዲሻሻል የተፈለገው? እንዲሻሻል የተፈለገበት ምክንያትስ ምንድን ነው?  እስከዛሬ ትክክል በመሆን ሲሠራበት ኖሮ አሁን ስህተት መሆኑ በምን ታወቀ? ይሻሻል የተባለው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት የተሻለና ትክክለኛው ቢሆንስ?…› የሚሉ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ‹የሚሻሻለው የቤ/ቱ ሥርዓት የዶግማዎቹን አይነኬነት ያረጋገጠ ነው ወይ?› የሚለው ጥያቄም መሠረታዊና ሊታለፍ የማይችል መልስ ፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ተነስተው አግባባዊ መልስ ካገኙ ሥርዓትን ማሻሻሉ ስህተት አይሆንም፡፡ ‹እውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ በዚህ መልክ ነው ወይ?› የሚለውን ጥያቄ ወደ ኋላ እናየዋለን፡፡

በሌላ በኩል በሦስተኛው አማራጭ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱን ማደስ ያስፈለገው በታሪክ ስህተት የሆኑ አስተምሆሮዎች ቀይራ ወይም ጨምሯ በመገኘቷ ነው የሚል መከራከሪያ በተሐድሶዎች ሊነሣ ይችላል፡፡ ይህም ቢሆን አንደኛ ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ ነው፤ ሁለተኛም በታሪክ የተፈጠረ ስህተትን ማሻሻልና ማስተካከል የሚቻለው ስምምነት ላይ ሲደረስበት ነው እንጂ በአቋራጭና በቅሰጣ እስትራቴጂ አይደለም፡፡ ለምሳሌም ‹በቤተ ክርስቲያኒቱ የተፈጠረው ትውፊታዊና ታሪካዊ ስህተት ምንድን ነው? ከመቼ ጀምሮ? ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ምንድን ነው? ትውፊታዊና ታሪካዊ ስህተት ስለመፈጠሩ ማረጋገጫችን ምንድን ነው? እስከዛሬ ተደብቆ ኖሮ ዛሬ እንዴት ሊታወቅ ቻለ? ምናልባት ስህተቱ የአሁኑ ቢሆንስ?…› እነዚህና መሰል ጥያቄዎች ተነሥተው መልስ ማግኘት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች የአስተምህሮ የዘር ሀረግ አላቸው፡፡ እና ቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርቷ በጊዜ ሒደት መሣሣቱን የሚያሣውቀውን ማስረጃ ተሐድሶ በነማን የዘር ሐረግ አገኘው? እነሱ እንደ ትክክለኛ ወስደው እናድስበት የሚሉት ትምህርት በክህደታቸው አውግዛ ከቤቷ የለየቻቸው መናፍቃን አስተምህሮ ቢሆንስ? እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ የሚፈልጉትም የተሐድሶ እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ተነሳሽነት የውስጥ አስተምህሮትዋን መሠረት አድርገው የተነሱ ከሆነ ነው፡፡ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጪ ባሉ ኃይሎች ቀስቃሽነት የራስዋን አስተምህሮ መሠረት ሳያደርግ የተነሳ ከሆነ ክርክሩ በሌላ አንግል ይሆናል፡፡

‹የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጭ ባሉ ኃይሎች አነሣሽነት ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመለወጥ የሚንቀሳቀስ ወይም ከውስጥና ከውጭ ባሉ አካላት ስምምነት የተፈጠረ እንቅስቃሴ ቢሆንስ ምን ዓይነት የክርክር አቋም ይኖራል? አሁን የሚካሔደው የተሐድሶ እንቅስቃሴስ ምንጩ ከየትኛው እንደሆነ እንዴት እናውቃለን?› የሚሉ መከራከሪያዎችን እንመርመርቻው፡፡ ከሁሉም በፊት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ውጭ ባሉ የዕምነት ተቋማት የተመሠረተ ድርጅት ነው ካልን በየትኛው ተቋም አነሣሽነት እንደተመሠረተ በዶግማ አሥተምህሮውና በእንቅስቃሴ ግንኙነቱ ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ከኦ/ተ/ቤ/ክ ውጭ ያሉት ሁሉም የዕምነት ተቋማት በኅበረት ተስማምተው ተሐድሶን አቋቁመው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ አስርፀው አስገቡት ብሎ ለማመን ይከብዳል፡፡ በተለይም እርስ በራሳቸው የማይስማሙ የእምነት ተቋማት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ለማደስ ኅበረት ፈጠሩ ማለት የማያስከድ ዕይታ ይሆናል፡፡ ደግሞስ የኢ/ኦ/ቤ/ክን ሃይማኖት ለማደስ የሚስማሙበት ምክንያት ምንድን ነው? ቢሆንስ ለምን በስውርና ምዕምናና አገልጋይ ካህናት ሳይውቁት ይህንን ያደርጋሉ? መንፈሳዊና ክርስቲያናዊ አካሔድ ነው? የሕግ አግባብስ ይኖረዋል?  ነው ከቤተ ክስርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ተስማምተው ነው ይህንን የሚያከናውኑት? ምክንያቱም ‹ተሐድሶ ከላይ ካሉ ‹አባቶች› ጀምሮ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ለማካሔድ እየጣረ ነው› የሚባል ሐሜት ስላለ ስምምነት ያደረጉ ‹አባቶች› ካሉ ብዬ ነው፡፡ ይህ ከሆነም ‹ምን ማለት ነው?› ከመንፈሳዊነት አንጻር ስናየው የሃይማኖት ልዩነት የለም ለማለት ነው? አዎ ከተባለም ኢየሱስ ክርስቶስን ፍጡር ማለትም ሆነ ፈጣሪ ማለት ትክክል ነው ማለት ነው? አሁንም አዎ ከተባለ እንደዚህ ከሆነ ለምን በሃይማኖት ማመን ያስፈልጋል? የሁሉም እምነት ትክክል ከሆነ  አለማመንም ትክክል የማይሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? በሃይማኖትም አለመመራት ትክክል ነው ከተባለ ነገሩ ከመንፈሳዊነት ወጥቷል፡፡ ሃይማኖት አልባነት ትክክል ከሆነም ተሐድሶ ስሑት ሊሆን ይችላል? አይችልም፡- ሃይማኖትን የማጥፋት ወይም የማርገብ ዓላማ አካል ነውና፡፡

ከዚህ በላይ የቀረበውን መከራከሪያ በማጥበብ ‹የተመረጡና ተቀራራቢ አስተምህሮ ያላቸው የሃይማኖት ተቋማት በጋራ የመሠረቱት ነው፤  ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚመሩ የእምነት ተቋማት ልዩነታቸው የተረጓጎም ነው፤ ስለዚህ ተቀራርበው በመነጋገር ወጥ የሆነ የሚያግባባ አስተምህሮ ለመቅረፅ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡› የሚል የመከራከሪያ ግምት ሊቀርብ ይችላል፡፡ ይሁንና ይህም ቢኾን አያስኬድም፡፡

ምክንያቱም፡-

አንደኛ የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚካሔደው በኦርቶዶክስ ቤ/ክን እንጂ በሌሎቹም ጭምር እየተካሔደ መሆኑን የሚጠቁም ማስረጃም ሆነ መረጃ የለም፡፡ ‹ተሐድሶ ነኝ› የሚለው ቡድንም እንቅስቃሴውን የሚያደረገው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ መሆኑን ነው በጽሑፎቹ ያረጋገጠው፡፡

ሁለተኛም አንድምታው እስከዛሬ የተካሔዱ የአባቶች ጉባኤያትን ሁሉ ይቃወማል፡፡ ለምሳሌ የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ፣ የፕሮቴስታንት (መካነ ኢየሱስ፣ የወንጌላዊያን አቤያተ ክረርስቲያን ኅብረት፣…) ሁሉም የእምነት ተቋማት ተስማምተው አንድ አስተምህሮ ሊኖራቸው ከቻለ ከኒቂያ (ሠለስቱ ምዕት) ጀምሮ የተደረገ ጉባኤያትና በጉባኤያቱ የተደረጉት ውግዘቶች የተሣሣቱ ለመሆን ይገደዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ አጠቃላይ የክርስትና ታሪክን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል፡፡ በሌላ አንግል ካየነውም በመጀመሪያ እስከ 4ኛው መ/ክ/ዘ ያሉ ጉባኤትን ኹሉም አቤያተ ክርስቲያናት በትክክልነት የሚቀበሉ ከሆነም የኦርቶዶክስን አስተምህሮ (ዶግማ) መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትመራበት ዶግማ እስከዚያ ጊዜ ድረስ የተወሰኑ ውሳኔዎችን መሠረት ያደረገ ነውና፡፡ ለዚህም የአባቶችን አስተምህሮ ሰብስቦ የያዘውን ሃይማኖተ አበው የሚለውን መጽሐፍና የቤተ ክርስቲያኒቱን ቅዳሴያት ማየት ጥሩ ምስክር ይኾናል፡፡

ሦስተኛም እንቅስቃሴው የሚካሔደው በስውር ስለሆነ የየእምነት ተቋሟቱን ምዕመናንና ካህናት የሃይማኖት ነፃነት የሚጋፋ ነው፡፡ ለምሳሌ አኔ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በዶግማዋና በሥርዓቷ ስንዱ እመቤት እንደሆነች አምናለሁ፤ እና ይህንን የማምንበትን ቀይረው ለምን እምነት አልባ ሊያደርጉኝ ይፈልጋሉ?

አራተኛም ‹ሁሉም ልክ ነው› ወይም ‹ሁሉም ስህተት ነው› የሚል መርህን የተከተለ ይመስላል፡፡ ይህ ከሆነም መሠረት አልባነት ነው፤ ምክንያቱም ሁሉም ትክክል ከሆነ ስህተት የሚባል የለም ማለት ነው፤ ሁሉም የተሳሳተ ከሆነም ትክክል የሚባል መሠረት አይኖርም፡፡ ይህ ደግሞ ከሃይማኖት ያለፈም አደጋ አለው፡፡ ሃይማኖትን የተወሰኑ ግለሰቦች የጉባኤ ስምምነትና ፍላጎት ማንፀባረቂያ በማድረግ ግቡን የሳተ ያደርጉታል፡፡ ይህ ምዕመናንን ለኢ-አማንያን አሳልፎ መስጣት ነው፡፡

እነዚህ የእምነት ተቋማት በስምምነት ተሐድሶን ማቋቋማቸው የማያስኬድ ከሆነም ይህንን ቡድን በስውርና በምሥጢር የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የሚፈልግ ድርጅት ወይም የሃይማኖት ተቋም ያቋቋመው ነው የሚል ጥርጣሬ መያዝ የግድ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አሁን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከውስጥ ሊነሣ የሚችልበት አግባብ ከሌለ፤ ከውጭ ያሉ የእምነት ተቋማትም በመስማማት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ለማደስና ለማረም የማይችሉ ከሆነ፣ የተሐድሶ እንቅስቃሴ መኖሩ ደግሞ እርግጥ ከሆነና ይህንንም የሚያከናውነው በስውር ከሆነ ይህንን እንቅስቃሴ በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ይዞ የሚያሽከረክረው ድርጅት አለ ብለን መገመታችን አግባብ ይሆናል፡፡ አሁን እንብርቱ ጋር ደርሰናል፤ የተሐድሶ የሚያስወናጭፋቸው (ይታደሱልኝ በማለት) ያቃላት ድንጋዮች ከየት እንደሆኑ እያነጻጸሩ ማየት ምንጫቸውን በሚገባ ያስረዳሉ፡፡ ይህ ሲሆን ነው ክርክሩን ከቤተ ክርስቲያኒቱ አውጥቶ ሜዳ ላይ የሚያደርገው፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመቀየር (በሌሎች የእምነት ተቋማት ከተመሠረተ ተሐድሶ አዳሽ ሳይሆን ለዋጭ ነው የሚባለው) ምክንያትና አግባብነትስ አለው ወይ? አግባብበነት ከሌለው እንዴት በማያገባቸው ቤ/ክን ላይ ተደራጅተው ለማደስ ይንቀሳቀሳሉ? በሕግስ ሊጠየቁ አይችሉም? ነው የኢትዮጵያ ሕግ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የመጠበቅ ኃላፊነት የለበትም? እኔ እንደሚገባኝ ከሆነ እንኳን የኢትዮጵያ ማንነት አስኳል የሆነቸውን ቤ/ክን እያንዳንዱ ዜጋም ቢሆን የሕግ ከለላ አለው? እና እንዴት ይህንን ያህል የታሪክና የባህል ማዕከል የሆነች ተቋም  ሌሎች ኃይሎች መፈንጫ ሰትሆን  ዝም ይባላል? ልብ ይበለሉኝ የተሐድሶው እንቅስቃሴ ከውጭ ወደ ውስጥ ከሆነ መቀየር እንጂ ማሻሻል አይደለም፡፡

ምናልባት የቤተ ክርስቲያኒቱም አባቶች ተስማምተውበታል ሊባል ይችላል፡፡ ይህም ቢሆን የበለጠ ችግርን ጎልጉሎ የሚያወጣ ይሆናል እንጂ የመፍትሔ መልስ የሚሰጥ አይደለም፡፡ አንደኛ እነዚህ የተመረጡ ‹የሃይማት ተቋማት አባቶችና ወንድሞች› የሃይማኖት ልዩነትን ለማጥፋት በመጣር እስከዛሬ ድረስ የተኖረበትን የክርስትና ሃይማኖት አስተምህሮ ገደል ይከቱታል፡፡ እንደገናም አስመሳይነትና አታላይነት የተጠናዎታቸው ናቸው፤ በተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚከናውኑት በሥውርና በሐሰት በመሸፈን ነውና፡፡ ክርስትና ደግሞ መንገዱ እውነት የሆነ የእውነት ጉልላት ክርስቶስን አካሉ ያደረገ ሃይማኖት ነው፡፡ እሱም በሐሰትና በማታላል አስተምሩልኝ ያለ አይመስለኝም፡፡ ‹ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቀረጣል› ብለው ነው እንጂ!

Please follow and like us:
error

8 COMMENTS

 1. አንተ ለመተንተን የሚከርከው ረጅም መንገድ ችግሩን ማወቅና ለችግሩ መፍትሄ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ከማሳየት ይልቅ የችግሮቹን ዓይነትና ጠባይ፣ ትስስሮሽና ፈለጎቹን በመመርመር በርን ጥርቅም አድርጎ መዝጋት ስለሚቻልበት የበላይነት ሃሳብን በመጠቆም የተደመደመ ነው።
  አንተ ስለ «ምስጢር» ትናገራለህ። አዲስ ኪዳን ምስጢር የተገለጸበት አዲስ ዘመን ስለሆነ ምስጢር የለም ብልህ ምን ልትለኝ ነው? ተሃድሶ? ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መሆን ማለት መጠየቅ፣ መረዳት፣ ተገቢ ምላሽ ማግኘት ወይም ማስረዳት የተከለከለበት ግን የሚነገርህንና የተነገረህን ብቻ ተቀብለህ የምትኖርበት ቤተክርስቲያን ማለት ነው? የምናምነው መንፈስን እንጂ የሚጨበጥ የሚዳሰስን ቁስ አይደለም።
  ምክንያቱም እግዚአብሔር መንፈስ ናውና።
  «በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና» ሮሜ 8፣14
  የእግዚአብሔርን መንፈስ የሚቃረን ክፉ መንፈስ ደግሞ በሰው ሊያድር ይችላል።

  «ማቴ12፥43 ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ፥ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም»
  ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን መንፈስ ልንመረምር ይገባል። የእውነት መንፈስ ወይስ የስህተት መንፈስ? ኦርቶዶክስ ቢሆን ካቶሊክ ወይም ፕሮቴስታንት አለያም ቺንቶይዝም ወዘተ ሁሉ ለራሱ ትክክል ነው። አማኙም የሚያምነው ከሌላው በተሻለ የርሱ ብቻ በሚያመልከው አምላክ ዘንድ የተወደደ መሆኑን የማይናገር ይመስልሃል?
  እንደክርስትና የምንመራበትን መንፈስ የሚወስነው ሰው ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። የስህተት መንፈስ መጽሐፍ ቅዱስን በስህተት እየተረጎመ አንዱ መንፈስ ብዙ የስህተት አብያተክርስቲያናትን አልተከለም? ጌታ አንድ ነው። እነዚህ ግን ብዙ ጌቶችን ለራሳቸው አበጁ። በእድሜ ረጅሞች ናቸው። እድሜ ለእውቀት ቢጠቅምም በራሱ ግን እውቀት አይደለም። ቢሆንማ ኖሮ ድንጋይን የሚበልጠው አልነበረም።
  ስለዚህ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስህተት መንፈስ የስህተት አሰራር አላስገባም ብለህ አትወራረድ! ቤተክርስቲያን የምትተዳደረው በሰዎች ነው። ክርስትናው በሰዎች ልብ ውስጥ እንጂ በህንጻው ውስጥ የሚቀመጥ ቅርስ አይደለም። ከላይ እንደገለጽኩት ሰዎች ደግሞ በስህተት መንፈስ ሊወድቁ እንደሚችሉ ስለምንረዳ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሳሳት የሚችሉ ሰዎች አልተፈጠሩም ልንል አንችልም።
  ቁም ነገሩ የተወለድንባት፣ ያደግንባትና ያለንባት ቤተክርስቲያን
  1/ ከወንጌል ቃል ውጪ የሆነ ወይም የሚቃረን አስተምህሮ አለ ወይ?
  2/ ሐዋርያት፣ ሊቃውንትና አበው መምህራን ካስተማሩትና ካኖሩት የተጨመረ ወይም የተቀነሰ አለ ወይ?
  3/ ቤተክርስቲያን ዘመኑን የሚዋጅ፣ ልጆቿን ባሉበት የሚያጸና ሥርዓትና አስተምህሮ አላት ወይ?
  4/ ቤተክርስቲያን የሐዋርያትን፣ የሊቃውንትን ትምህርትና መሠረት የተቀበሉ በእውቀት፣ በቅንነትና በነጻነት የጸኑ ሰባክያን፤ መምህራን አላት ወይ?
  5/ የመንፈስ ቅዱስን ጥሪ የተቀበሉ፤ እንደመንፈስ ቅዱስ ሃሳብ የሚኖሩ፣ ስለመንጋው የሚገደው የቤተክርስቲያን አመራር አካል አለ ወይ?
  ብለው የሚጠይቁ ድምጾች አለባት። ድምጾች ሁሉ ጥሩ ናቸው ባይባልም ድምጾቹን መለየት፣ መልስ የሚያሻው ወይም ውድቅ የሚሆነውን እንደዓይነቱ መመለስ እንጂ ድምጽ አልሰማም ብሎ ጆሮን መያዝ መፍትሄ አይደለም። ጆሮ ያለው ይስማ ተባለ እንጂ ይድፈን አይደለም።

  ከዚህ አንጻር በዚህ ዘመን በክርስትናቸው ቢጠይቁ ወይም ምላሽ ቢሹ ወይም መንፈስ ከእውነት እንደሆነ ቢመረምሩ ልጆቿን መናፍቃን ወይም ተሃድሶ ማለቱ የችግሮች መፍትሄ አይደለም።
  «በከተማዎችም ሲዞሩ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የቈረጡትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ሰጡአቸው» የሐዋ 16፣4
  ሥርዓት ይሰራል፣ ይከበራል እንደዚሁ ሁሉ ሊጣስ ይጥላል። እንዳይጣስና ይጠበቅ ዘንድ የሐዋርያትና የሽማግሌዎች ሥርዓት መታወቅ አለበት። መነሻና መድረሻ አለው። መጠበቅ ካለበት እንዴትና በማን? ጆሮ ጠገብ ሁሉ የሚያከርበት(beyond its border) የሚናኝበት መሆን የለበትም።
  ሳጠቃልል ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ተቀናቃኝ እንዳለባት አምናለሁ። እንኳን ከራሷ ልጆች ፣ተቀናቃኞቿ የሚያነሱባትን ሃሳብ ሁሉ ከተቀናቃኝ ስለመጣ ብቻ ውድቅ ልናደርገው አይገባም። ጠላት የሚያነሳቸው ሃሳቦች እሱ የሚያሸንፍበትን መዝ’ዞ ቢሆንም ሳያውቀው አስተማሪ ሆኖ ሊገኝ ይችላል።
  «መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው» ሰይጣን ለማሳሳት ይህንን ቃል ለጌታ ተናገረ። ሳያውቀው ግን ይህን በመናገሩ እኛ ይህንን ትምህርት ቀሰምን። «ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው» ማቴ 4፣6-7 የተነሳውን ሃሳብ መመርመርና ምልሽ መስጠት።

 2. አንተ ለመተንተን የሚከርከው ረጅም መንገድ ችግሩን ማወቅና ለችግሩ መፍትሄ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ከማሳየት ይልቅ የችግሮቹን ዓይነትና ጠባይ፣ ትስስሮሽና ፈለጎቹን በመመርመር በርን ጥርቅም አድርጎ መዝጋት ስለሚቻልበት የበላይነት ሃሳብን በመጠቆም የተደመደመ ነው።

 3. I am satisfied by the penetrating insight the above article has delivered to the reader. The writer has done a remarkable detective job that has closed in on the principal criminal that vies to colonize the spiritual mind of Ethiopians. God bless you.

 4. I am satisfied by the penetrating insight the above article has delivered to the reader. The writer has done a remarkable detective job that has closed in on the principal criminal that vies to colonize the spiritual mind of Ethiopians. God bless you.

 5. First of all,these are the basic questions one should ask when talking about religion, particularly Christianity.
  1/ ከወንጌል ቃል ውጪ የሆነ ወይም የሚቃረን አስተምህሮ አለ ወይ?
  2/ ሐዋርያት፣ ሊቃውንትና አበው መምህራን ካስተማሩትና ካኖሩት የተጨመረ ወይም የተቀነሰ አለ ወይ?
  3/ ቤተክርስቲያን ዘመኑን የሚዋጅ፣ ልጆቿን ባሉበት የሚያጸና ሥርዓትና አስተምህሮ አላት ወይ?
  4/ ቤተክርስቲያን የሐዋርያትን፣ የሊቃውንትን ትምህርትና መሠረት የተቀበሉ በእውቀት፣ በቅንነትና በነጻነት የጸኑ ሰባክያን፤ መምህራን አላት ወይ?
  5/ የመንፈስ ቅዱስን ጥሪ የተቀበሉ፤ እንደመንፈስ ቅዱስ ሃሳብ የሚኖሩ፣ ስለመንጋው የሚገደው የቤተክርስቲያን አመራር አካል አለ ወይ?
  I would like to forward these questions to anyone who would like to think about the Ethiopian Tewahido Church. One can not be orthodox because he/she says so. No. It is what you believe in and what you practice which can only make you deserve the title.

  Second, in your article I read extremist nationalism (one of the burdens of eastern Churches) mixed with logical arguments which are loaded with theological ignorance. I don’t blame you for that because you are just part of the culture where anyone without sufficient theological background can label a person heretic. You don’t even seem to know the difference between schism and heresy.

  • ለእኒዬ! መጀመሪያ ስለሰጡኝ አስተያየት እግዜር ይስጥልኝ፡- ሌሎቹንም አስተያየት ሰጪዎች እንደዚሁ፡፡ በሰጡት አስተያየት ውስጥ የማልስማማባቸው ነጥቦች ስላሉ በጥቅሉ ግብረ መልስ ለመስጠት ተገደድኩ፡፡ ከሁሉም በፊት ግን ለጠየቋቸው ጥያቄዎች መልሶችን ወይም ላቀረብኳቸው ሐሳቦች ማርከሻ ነጥቦችን አንስተው ከዚያ በኋላ ወደ ራስዎ አስተያየት ቢገቡ ኖሮ መልካም ይሆን ነበር፡፡ ግን ያ የእርስዎ ፍላጎት ስላልሆነ ወይም በሌላ ምክንያት ወደ ጎን አንጓለው ‹ እንዲህ ነው የሚጠየቀው› ብለው አሉኝ፡፡ ግን ልጠይቀዎትና የእኔ ጥያቄ ስህተቱ ምኑ ላይ ነው ይላሉ? እኔ እኮ ያቀረብኩት አሳብ፡ 1. ተሐድሶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከውስጥ ሊፈልቅ የሚችልበት ምክንያት የለውም፤ 2. ከውጭም የተለያዩ አቤያተ እምነቶች ተባብረው ወደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚያስገቡበት አግባብ የለም፤ አቤያተ እምነቶቹ ተስማምተው ያቋቋሙት ወይም አንድ ልዩ ተልኮ ያለው አካል አስርጎ ያስገባው ከሆነም ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመለወጥ (ለመውረስ) ያለመ እንጂ ጤነኛ አይደለም የሚል ነው፡፡ ይህንን እንዴት ያዩታል? እርስዎስ ከየትኛው ነዎት ከተሐድሶ ካምፕ ወይስ ተሐድሶዎችን ከማይቀበሉት አምባ ወይስ ከሁለቱም የሉበትም? ዝም ብለው ለአስተያየት የቋመጡ እንደማይሆኑ ግምቴ ነው፡፡
   አሁን ደግሞ ወደተከበረው አስተያየትዎ ልግባና! ያነሷቸው ጥያቄዎች መሠረታዊ የክርስትና እምነት መመዘኛዎች መሆናቸው አውነት ነው፡- ጥያቄዎቹን ማሾም አንስተዋቸዋል፡፡ጥያቄዎቹ የተሐድሶን መሠረታዊ አስተምህሮ ለመተንተንና ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተነሳ ከሆነ ብቻም በዚህ ክልል ውስጥ ሆኖ ለመመዘን ይረዳሉ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ የተሳሳተ ትምህርት ይዛ መጥታለች ብሎ ቀድሞ ለገመተ ሰውም ይሠራሉ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ተሐድሶ ውጫዊ ሰርጎ ገብ ከሆነ ግን፤ እውን እርስዎ ያቀረቧቸው የክርስትና ሃይማኖት መመዘኛዎች አግባብ ይመስሎዎታል? ለእነዚህ እርስዎ ለጠየቋቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ያለን እኛ ነን የሚሉ በአሜርካ ብቻ ከ22 ሺህ በላይ የክርስትና እምነቶች መኖራቸውን አያውቁም እንዴ? ነው ሁሉም ልክ ናቸው ሊሉ ነው? ሁሉም ትክክል ከሆኑ ለምንስ ጥያቄውን ማንሳት ያስፈልጋል? ለመሆኑ በየትኛው የክርስትና መነፅር ነው የሚመዝኑት? የፕሮቴስታንቶች መመዘኛ ለኦርቶዶክሶቹ ስህተት ያለበት መሆኑን በተቃራኒው የኦርቶዶክስ አስተምህሮ በፕሮቴስታን ካምፕ ላሉት ሁሉ ተረት ነው እንደሚባል አያውቁም እንዴ?
   በሁለተኛነት ያነሱት ሁለት ነጥቦችን ነው፡፡ አንደኛው ሀገራዊ ስሜት ከሃይማኖት ጋር ተደባልቆ ይዞሃል ዓይነት አሳብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ‹የሥነ መለኮት ዕውቀትህ አልበሰለም› ዓይነት ማጣጣል ነው፡፡ ሰለ ሁለቱም ነጥቦች ያቀራረበዎ መንፈስ ይገባኛል፡- እንኳን ይችን… ፡፡ ስለ መጀመሪያው ልጨምርለዎትና ነጮች በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ በሃይማኖት ተከልለው የሚያድርጉት የሁለዓቀፍ፣ የባህልና የማንነት አጠባም አይስማማኝም፡፡ የተሐድሶ የቀበሮ ጉድጓድ ውጊያም በዚህ መልክ ታጥቆ መሆኑን የርስዎን ያህል ወይም በውስጥ ገብቼ የውሎና አዳሩን ሁኔታ በጥልቀት ባልረዳም ካፈጣጠሩ፣ ካካሃዱ፣ ከግቡና ካላበት ደረጃ አንጻር እገነዘብለታለሁ፡፡ ስለሁለተኛ ነጥበዎ- የሥነ መለኮት ደናቁርት ነህ ላሉት፤ እንደመሰለዎ ይሁንለዎ! ወይ በመመዘኛዎ ሁኔታ ወይም በ‹እስኮላርሽፕ› ሥነ መለኮት ትምህርት በመብሰልዎ ይሆናልና፡፡ ምናልባት ወደፊት በተሐድሶ ዙሪያ ሥነ መለኮታዊ ትንታኔ አዘጋጅቼ ሳቀርብ በሚሰጡኝ አስተያየት የእርስዎን ሊቅነትና የኔን ድንቁርና ሌሎች ይፈርዱት ይሆናል፡፡ ለማንኛውም ይህ ነጥብ ይቆየን!

 6. First of all,these are the basic questions one should ask when talking about religion, particularly Christianity.

Leave a Reply