ንጉሥ ማራኪ!

 

‹መሬት የእግሬ መረገጫ ናት› ስላለ

እግሩን ዘርጥጬ ልጥለው፣

‹ሰማይ ዙፋኔ ነው› በማለቱም

አልጋውን ልገለብጠው

ስታገል፣ ስታገል፣ ስታገል፤

እግሩ መሬቱን ሞልቶት

አልጨበጥህ ቢለኝ፣

ዝፏኑም ያለቅጥ ገዝፎ

ለመገልበጥ ቢያስቸግረኝ፣

ተስፋ ቆርጬ ልተው ስል፤

አገኘሁት! አገኘሁት! አንቺ ዘንድ ተሸጉጦ፣

ለካ አልጋውን ነቅንቄበት ከሆድሽ ገብቷል ደንግጦ፤

ማሪያም ሆይ! እንዳትለቂው በሥጋችን ይዠሻለሁ፣

መማረኩንም ንገሪው፣

መሔጃ የለህም በይው፣

‹ንጉሥ ማራኪ› ብዬ እፎክርበታለሁ፡፡

Please follow and like us:
error

2 COMMENTS

  1. በጣም ጥሩ ሥራ ነው። እባክዎን ብዙ ይጻፉ እንዳያቋርጡ። ትውልዱ ማንነቱን፣ ታሪኩን፣ ባህሉን እንዲያውቅ እንዲህ ከስር ከምንጩ የተቀዳ እውቀት ወደዘመነኛው መድረክ (ኢንተርኔት/ዲጅታል ቴክኖሎጂ) መምጣት አለበት።

  2. በጣም ጥሩ ሥራ ነው። እባክዎን ብዙ ይጻፉ እንዳያቋርጡ። ትውልዱ ማንነቱን፣ ታሪኩን፣ ባህሉን እንዲያውቅ እንዲህ ከስር ከምንጩ የተቀዳ እውቀት ወደዘመነኛው መድረክ (ኢንተርኔት/ዲጅታል ቴክኖሎጂ) መምጣት አለበት።

Leave a Reply