ቅንጭብ፡- ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥበብን ሲገልጽዋት

…የልብ ሥሯ ወዲያና ወዲህ በማለት መቅበዝበዝ ሳይኖርባት መጽናት (መታገስ) ነው፤ የዕውቀትም ሥሯ ማመስገን ሲሆን ፍሬዋ ዕረፍትና ሰላም ነው፡፡ (አንጋረ-ፈላስፋ፣ ገጽ-22) የዕውቀት ሥር መሠረቷ ሃይማኖት፣ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ለሰው ሁሉ ባሕርየ-መልካም መሆንና ከወንድም ከጓደኛም ጋር መፋቀር ነው፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ-34)

… መጻሕፍት የጥበብና የአእምሮ መዝገብ ናቸው፤ አእምሮም የነፍስ መኖሪያ ቦታ ናት፤ ነፍስም የማስተዋል ኃይል ናት፡፡ ሰው ሁሉም ክብር ሥጋዊና ክብር መንፈሳዊ የሚያገኘው በአእምሮና በጥበብ ነው፡፡ …ጥበብ እንግዳ በመሆን ጊዜ ወዳጅ ጓደኛ ናት፤ በዐደባባይም ግርማ ሞገስ ናት፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ-8-9) ጥበብ ከማር ትጣፍጣለች፤ ከሱኳርም ትመረጣለች፤ ከሷ የቀመሰ ጨምሩልኝ! ጨምሩልኝ! ይላል እንጂ በቃኝ ጠገብሁ አይልም፤ ዕድሜውን ሁሉ ሲመገባት ቢኖር እንኳ አይሰለቻትም፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ- 48) 

ከአእምሮ የበለጠ መዝገብ ከእውነት የቀና መልክተኛ የለም፤ ከእውነት የበለጠ መንገድ መሪ፣ ዝም ከማለት የበለጠ ጠባቂ የለም፤ መናገር እንኳ ብር ቢሆን አለመናገር ወርቅ ነው ተብሏል፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ- 48)

እውነት ብንወድም የፍጥረት ሁሉ አስፈላጊና ተገቢ የሆነውን በእርሱ እንድናይበት እግዚአብሔር በሰጠን በልቦናችን ውስጥ እንፈልጋት፡፡ (ዘርአ ያዕቆብ፤ ሐተታ-ዘዘርአ ያዕቆብ፣ ገጽ-25)
‹ለጠቢብ ጥበብን እንዲጨምርለት ምክንያት ጨምርለት› የተባለውን ሰምታችኋል፡፡ (ወ/ሕይወት፤ ሐተታ ዘወልደ-ሕይወት፣ ገጽ 45) ጥበብና እውነት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፡፡… ፀሐይ የብርሃን መሠረት እንደ ሆነ እንዲሁ እግዚአብሔርም የጥበብ መሠረት ነው፡፡ መንፈስ የሕይወት ምንጭ እንደ ሆነ እንዲሁ እግዚአብሔርም የእውነት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ፣46) መመርመር ወደ ጥበብ የምንገባበት በር ነው፡፡ ዕውቀትም ይህን በር ከፍተን ወደ አዳራሹ ምሥጢር ገብተን ከጥበቡ መዝገብ የምንካፈልበት እግዚአብሔር የሰጠን ቁልፍ ነው፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ፣47) ሁሉን መመርመር መልካም ጥበብ ነው፤ ነፍስ ነባቢትና መርማሪ ዕውቀትን ለሰጠን እግዚአብሔርም ያስመሰግነዋል፤ እምነት ግን ሳይመረመርና ከዓዋቂ ተፈጥሮ ባሕርይ ጋር ሳይስማማ ማመን የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ፣53)

ደንጋይና ጭቃ ቢቀጣጠሉ ታላቅ ቤት፣ ረጅም ቅጥር ይሆናሉ፤ እናንተም መሬታዊያን ሰዎች እንደዚህ ብትረዳዱ ጥበባችሁና ኃይላችሁ ከሰማይ በደረሰ፡፡ (አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ፤ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ፣ ገጽ-1) ጥበብን ለምን ትፈልጓታላችሁ? ከገበያ አትገዛ? ከምድር አትበቅል? ከኪሩቤል ጀርባ ካለው ከሕይወት ምንጭ በሃይማኖት ብርጭቆ ቅዱ፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ-8)

እግዚአብሔር አብ ጣት ነው፣ እግዚአብሔር ወልድ ብዕር ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ቀለም ነው፤ ሰማይና ምድር ወረቀት ናቸው፤ ፊደሉም ፍጥረት ነው፤ እግዚአብሔር አብም በቃሉ ሰማይንና መሬትን ፈጠረ፤ ያለባቸውን ፍጥረት ሁሉ ፈጠረ፤ በመንፈሱም አጠናቸው፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ-14)
የዚህን ዓለም ሥሩን አገኛለሁ ብዬ ቆፈርሁት፤ ጽኑም ድንጋይ ሆነብኝ ድጅኖ አሳቤም ሁሉ አለቀ፤ እንዲያው ባየው ባስተውለው ሥሩ እግዚአብሔር ነው፡፡ (ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ-15)

Please follow and like us:
error

Leave a Reply