የሐዘን እንጉርጉሮ ከያዙ ቅንጫቢ ኢትዮጵያዊ ቅኔዎች

1

ሽህ  ብረት በፊቱ የሚደባለቀው፣

‹የዳሞት›ን መንገድ ብቻውን ዘለቀው፡፡

2

እንኳን ደኅና ገባህ ከሄድክበት አገር፣

ጠላቶችህ ሁሉ ይቅር ብለው ነበር፡፡

3

‹ትግራይ› አይደለም ወይ መለስ አገርህ፣

‹አክሱም› አይደለም ወይ መለስ ትውልድህ፣

የጁ ነው በማለት የደበደቡህ፡፡

4

ለጌታ አድሬ እንደዋዛ፣

አንዲት ላም እንኳን ሳልገዛ፣

ምን ይለኝ ይሆን ዘመድ፣

ወተት ብዬ ብሔድ፡፡

5

አገራችን ቆላ መስክ የለ ከደጅ፣

እንዲህ አፈር ላፈር እንጫዎት እንጂ፤

ከቆላ ሸንበቆው ማማሩ፣ ማማሩ፣

ቆርጠው ጣሉት እንጂ ለም አፍር እያሉ፡፡
6

‹መለስ ዜናዊ› ታላቅ መስፍን፣

ነበሩ ሲሉ ባገራችን፣

እንዲያ ሳያጡ ሰገነት፣

ምነው አደሩ ፈረስ ቤት፣

ሞከሩት እንጂ አልኖሩም፣

ከዳሞት አልቀሩም፡፡

7

በዓለ ድባብ ንጉሥ ባለ ጥና አቡን፣

እየዞሩ ፈቷት አገራችንን፡፡

8

አሁን ምን ያደርጋል ሱሰኛ መሆን፣

ብዙ ቤት ፈረሰ ትላንት በዚያ አቡን፡፡

9

ይድናል እያልን ዓይን ዓይኑን ስናይ፣

እንዲያ እንደፈራነው እውነት ሞተ ወይ?
10

ምን ዕዳ ነበር ቢቀር፣

ከዕዳ ሞት መፈጠር፡፡

11

ውዳሴ ማርያም ደግሜ

ተቀምጬ አደርሁ ደክሜ፤

በመቁጠሪያዬ ሳንቀላፋ፣

ዋ! መቋሚያዬ ጠፋ፡፡

12

የዛሬ ዘመን ወዳጅም፣

ከሽሕ አንድ አይገኝም፣

አንቱ ብትለው ይኮራል፡

አንተ ያልከው ግን ይኖራል፡፡

13

የዛሬን ዘመን ምስክር፣

አልጣራውም ይቅር፤

ምነ እኔን ያልኸኝ አባይ፣

ጊዜው አይአለም ወይ?

14

አሻግሬ ባይ መንገዱን፣

አረ ሰው ምናምን፡፡

15

ሞት ዕቃዬ ነው ብሎ፣

ወሰደው አሉ በቶሎ፣

ሌላውስ ይቅር ቢሻው፣

ዓይኑ እንኳን አሳስቶት በተወዉ፡፡

16

ተስቦ ገብቶ ከቤቴ፣

አልወጣ ብሎኝ ዓመቴ፡፡

17

ትንሹም ወይፈን ተጎዳ ትልቁም በሬ ደከመው፣

ወይፈን ታላገኘሁ በምን አርሼ ልብላው?

18

ንጉሥ የሠጡኝ ታላቅ ዕቃ፣

ላገር ለምድር የሚበቃ፣

አድጦኝ ወድቆ እስኪሠበር፣

ስይዘው ቀሎኝ ነበር፡፡

19

እዚያ ላይ ሆነህ ብትጠራኝ፣

አቤት እንዳልል ድምጥ የለኝ፤

እረ! የት ሆኜ ልጠብቅ

መምጫህ አይታወቅ፡፡

20

ከሚበልጠው ከሁሉ፣

እረ ተማሩ ብሉ፤

እናንተ ሰዎች አስተውሉ፣

ከዳ ከዳ አትበሉ፡፡

21

ወደ አደባባይ ወጥተህ፣

ከባላጋራህ ተሟግተህ፣

ክርክር ገጥመህ ወደ ማታ፣

ዓለም አፈር ነው ስትረታ፡፡

22

‹ዋልድባ› ወርጄ ቀስሼ፣

ልብሰ ተክህኖ ለብሼ፣

ታዩኛላችሁ እኔን

ነገ ገብቼ ሣጥን፡፡

23

መሬት ነስተውኝ ዘመዶቼ፣

እመቃብር ቤት ገብቼ፣

ከቶ ምን ይሆን የኔ ነውሬ፣

በሬሳ ላይ መኖሬ፡፡

24

ክፉ ቢናገር ተቆጥቶ፣

ጠላትህ ደሙ ፈልቶ፤

እሱም እንዳንተ ሰው ነው

እረተው ሰብቀህ አትውጋው፡፡

25

ዛሬማ ጠጅ ማ ጠጥቶ፣

ሁሉ ጠላ ቤት ገብቶ፡፡

26

እኔን ከፋኝ እንጂ አገሬን ምን ከፋው፣

ግራር አበቀለ ዝሆን የማይገፋው፡፡

27

ላም ገዝቼ ጥገት፣

እጠጣ ብዬ ወተት፣

ቅሉ ተሠብሮ አዝናለሁ፣

በምናልባት አለሁ፡፡

29

በምን ይበሏል ባዋዜ፣

ይህንን አልቦ ጊዜ፡፡

30

ቤት ሥራልኝ ብንለው፣

ዕንጨት መረጠ አናጢው፤

ሰው ሲያነሣ ሣንቃውን፣

አንተም አትተው ማዘኑን፡፡

31

ቀፎ አለ አሉ ባገርህ፣

እረ ተው ማር እባክህ፡፡

32

መተኪያ እንኳን ሌላ የለኝ፣

ጥላዬ ተሠብሮ አዝናለሁኝ፡፡

33

ሠሪው ፍጥረቱን አታለለ፣

በኖራ ሠራሁ እያለ፤

መች ይፈርስ ነበር ቤታችን

እውነት ኖራ ቢሆን፡፡

34

መልካም ፈረስ ጭነህ፣

ስትወጣ ስትወርድ አየንህ፤

ከሜዳ ስትደርስ ዝግ አድርገው

መቼም ጊዜው ጣይ ነው፡፡

35

ስማኝ ልንገርህ አትስነፍ፣

ተው እየሠራህ እለፍ፡፡

Please follow and like us:
error

18 COMMENTS

Leave a Reply