የአድዋ ማስታወሻ

1. ጎራው

ጎራው! አይደለም ወይ! ወኔ መቀስቃሻው ለአበሽ ጀግንነቱ፣

በጎራ አይደለም ወይ ጥንትስ ኢትዮጵያውያን የሠለጠንቱ፣

አድዋም ጎራ ነው ኢትዮጵያዊ ወኔ የከተመበቱ፣

ጎራን በመድፈር ነው ጣሊያን ያበቃለት የገባው ተቤቱ፣

የጎራ ላይ ልጆች፣ አረ! ጎራው በሉ፣ ጎራው ነው ውርስ ሀብቱ፡፡

(ካሣሁን ዓለሙ 22/06/06)

2. ክብሪቱ አድዋ!

ክብሪት ባይኾን ኖሮ አድዋ፣ የችቦ መለኮሻ፣

በአፍሪካ  ደመራን ባያበራ፣ ፀረ-ፀለምቱ ሐበሻ፤

ቦግ ብሎ  ሰውን ባያሳይ በዳፍንት ሲርመሰመስ፣

እንኳን የነፃነት ብርሃን ማየት፣ የኑሮውንም ጣዕም መቅመስ

ጥቁር ሰው ሳይታይ ቀርቶ፣

የማየት አቅሙም ተዘንግቶ፤

እንደታወረ በኖረ

ሰው መኾኑም በቀረ፤

ስለዚህ አድዋ ክብሪት ነው እሳትን ያፈለቀ፣

ጨለማው እንዲወገድ ብርሃን የፈነጠቀ፤

የጥቁር ሰውነትን  ሰው መኾን ያሳወቀ፡፡

(ካሣሁን ዓለሙ 23/06/06)

Please follow and like us:
error

Leave a Reply