የኢትዮጵያዊነት ምንነት መግለጫ

ከፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ

ኢትዮጵያዊ መኾን እጅግ የሚያኮራ ነገር መኾኑን ባለመገንዘባችን እና ‹ኢትጵያ› የሚለውን ቃል ትክክለኛ ፍቺ ባለማወቃችን፣ አንዳንዶቻችን በኢትዮጵያዊነታችን እናፍራለን፡ ‹ኢትዮጵያዊነት› ማለት ምን ማለት እንደኾነ ለማብራራት የቃሉን ትርጉም ምንጭ ማወቅ ግድ ይላል፡፡

‹ኢትዮጵያ› ማለት የቢጫ ወርቅ ሥጦታ (ለእግዚአብሔር ማለት) ነው፡፡ ይህ ስም የተሰጠው ለኢትዮጵያ መሥራችና የኢትዮጵያዊያን አባት ለኾነው ለኢትዮጵ ነው፡፡ እንግዲህ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ወርዶ፣ ወርዶ ወደ እኛ የደረሰው ከሱ ስም ነው ማለት ነው፡፡ ‹ኢትዮጵያዊ› ማለት በግሪክ ቋንቋ የተቃጠለ ፊት ማለት ነው የተባለው ነጭ ውሸት ነው፡፡ በግሪክ መዝገበ ቃላትም ወስጥ እንዲህ የሚል ቃል የለም፡፡

ኢትዮጵያውያንን ኹሉ አንድ የሚያደርጋቸው፣ ከፍ ሲል ኢትዮጵያን በስሙ ካስጠራው ከካህኑና ከንጉሠ ነገሥቱ ከኢትዮጵ፣ ዝቅ ሲል የሱ ዘር ከኾነው ከነቢዩና ከፈላስፋው ከደሸት መወለዳቸው ነው፡፡

ኢትዮጵ የዛሬ 4000 ዓመት አካባቢ ዐሥር ወንዶች ልጆች ወልዶ ነበር፡፡ ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፡፡ አቲባቢኦርተምናአቴርአሻንአክሲብበሪሳቴስቢቶላ እና አዜብ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ስሞች ውስጥ አሻን፣ በሪሳ፣ ቶላ እና አዜብ አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡

የኢትዮጵ ዘር፣ የነብዩ ደሸት ልጆች ደግሞ መደባይመንዲጂማ እና ማጂ ይባሉ ነበር፡፡ ማጂ ማራ (አማራ)ን እና ጃማን ወለደ፡፡ ሰዎች የተሰየሙት የዛሬ 3600 ዓመት ቢኾንም፣ እነዚህ ስሞች አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ፡፡

የኢትዮጵያ 10 እና (በተለይም) የደሸት 4 ልጆች ተባዝተው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በሞላ ኾነዋል፡፡ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ባሉት ትውልደ ኢትዮጵያውያን የደም ሥሮች ውስጥ የኢትዮጵና የደሸት ደም ይዘዋወራል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በሞላ ምንጫቸው አንድ እና አንድ ነው፡፡ ስለዚህም ቋንቋቸው ቢለያይም ደማቸው ዘራቸው አንድ ነው፡፡ ቋንቋ ደግሞ የመግባቢያ መሣሪያ እንጂ ዘርን አመላካች ወይም የዘር ክፍል አይደለም፡፡ ቋንቋ ማለት ጎሣ ማለት ነው፡፡

ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ጎሥአ (ገሣ) ልብየ ሰናይ ይላል፡፡ ልቤ መልካም ነገር ተናገረ ማለት ነው፡፡ አገሣ ወይም ከውስጥ አወጣ የተባለው ቃል ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ ጎሣ ማለት አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡ ዘር ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ አንድ እናት እና አባት ወደ ፈረንሳይ አገር ሄደው ልጅ ቢወልዱና ፈረንሳይኛ ቢናገር፣ ከዛም ወደ አሜሪካን አገር ተጉዘው ሌላ ልጅ ወልደው እንግሊዘኛ ቢናገር፣ ልጆቻቸው ኹለት የተለያዩ ቋንቋዎች ስለተናገሩ ወንድማማችነታቸው አይፋቅም፡፡ ወላጆቹም አማርኛ፣ ኦሮምኛ ወይም አፋርኛ በመናገራቸው ወላጅነታቸው አይደመሰስም፡፡ ደምና ዘራቸው አንድ ነውና፡፡ ስለዚህ ወሳኙ ቋንቋ ሳይኾን ደምና ዘር ነው፡፡ ስለዚህ ቋንቋ ወይም ጎሣ ወሳኝ አይደለም፡፡ መግባቢያ ነው እንጂ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ከ80 በላይ የሚናገሩ ጎሣዎች አሉ፡፡ ኾኖም እነዚህ ጎሣዎች በቋንቋ ቢለያዩም በደማቸው አንድ የኢትየጵያ ልጆች ናቸው፡፡ የሚያገናኛቸውም ኢትዮጵያን በስሙ ያስጠራው ኢትዮጵ አባታቸው ነው፡፡

ከ200 ዓመታት በፊት መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ይባል ነበር፡፡ የእዚህ ምክንንያቱ የኢትዮጵያ ተወላጆች በመላው አፍሪካ ተሠራጭተው፣ አፍሪካን አሠልጥነው ስለኖሩበት ነው፡፡ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን በቅኝ መግዛት ከጀመሩ ወዲህ ግን ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ቀርቶ አህጉሩ አፍሪስካውያን በተባሉት በአፋሮች አፍሪካ መባል ጀመረ፡፡ አሁን ድረስ ስሙ ከእኛ ስላልወጣ ቅር አንሰኝም፡፡

አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሰው በኹለት ምክንያቶች ኢትዮጵያዊ ይኾናል፡፡ አንደኛ ኢትዮጵያ ውስጥ በመወለዱ፡ ኹለተኛ፣ ተውልደ ኢትዮጵያዊ በመኾኑ፡፡ ኹለቱንም የሚያገናኛቸው በደምና በዘራውቸው ከኢትዮጵ መውረዳቸው ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊ ማለት በዓለም ልዩ የኾነ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ ዮጵ የተባለ ቢጫና ብርቅዬ ወርቅነት ማለት ነው፡፡ ከዚህም በላይ፣ በዓለሙ ፈጣሪ ለእግዚአብሔር ብቻ የሚቀርብ ልዩ ገጸ በረከት ማለት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የሕይወት ምንጭነት፣ የስብእና መገኛ ሥፍራ ማለት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የሥነ መለኮት ከፍታ፣ የሥልኔ መጀመሪያ፣ የሰው ዘር አርአያ፣ የሥነ ምግባር ልዕልና ማለት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የሀርነት፣ የጀግንነት እና የፍትሐዊነት ተምሳሌት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማት የእኩልነትና የሰው ልጅ ክቡርነት ዓርማ ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የታማኝነት እና የተአማኒነት እንዲሁም የመለኮት ማኅደርነት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የፅናትና የብርታት እና የትግእሥትና የዘላቂነት ምልክት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለትየሀቀኝነትና የእውነተኛነት ምሳሌ ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የርህራሄና የቸርነት ናሙናነት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማት ሰው አክባሪነት፣ እንግዳ ተቀባይነት፣ ይሉኝተኝነት እና አዙሮ ተመልካችነት ነው፡

 • ኢትዮጵያዊነት የጥበበኝነት ቁንጮ፣ የብልኅነት እራስ ማለት ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የቅድስና እና የብፁዕነት ጫፍ ነው፡፡

 • ኢትዮጵያዊነት ማለት የወንድማማችነትና የእህትማማችነት የተመዛዘነ ማንነት ነው፡፡

         ይቀጥላል….

(ስውሩና ያልተነገረው የአይሁዳውያን እና የኢትዮጵያውያ ታሪክ፤ ገጽ 222-233)

Please follow and like us:
error

1 COMMENT

Leave a Reply